2 869 855 libros electrónicos en 110 idiomas
¿No le conviene? No hay problema. Puedes devolver los artículos hasta 30 días
No se equivocará con un vale de regalo. El destinatario puede elegir cualquier producto de nuestra oferta.
"ፍለጋ" የተሰኘው ይህ የባለ ሦስት ቅጽ እኔ በእንተእኔ ሁለተኛ ጥራዝ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የየመን ሙዋላዲኖች (በውጭ ሀገራት ተወላጅ የሆኑ የመኖች) ለእኩል መብትና ለዜግነት ፍቃድ ስለሚያደርጉት ትግል ያወሳል። መሃይምነትና ተከታታይ የጎሳ ግጭቶች ልማትንና ዘመናዊነትን በማጨናገፍ፣ አሁንም ሀገሪቱንና አካባቢዋን በማወክ ላይ ናቸው።
ወደ ቅድመ አያቶቹ ምድር በተሰደደ አንድ የአሥራ ስድስት ዓመት ልጅ ተጋድሎ ውስጥ፣ የየመንን መሠረታዊ መገለጫዎች ፍንትው አድርገው ለመረዳት ይገድዎታል? እንግዲያውስ ይህ የእርስዎ መጽሐፍ ነው።
በምድር ላይ ካሉት ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዱ የነበረውና፣ የአረብ ሥልጣኔ መገኛ የሆነው፣ የንጉስ ሰሎሞን እንግዳ በነበረችው በመጽሐፍ ቅዱሳዊቷ በንግሥተ ሳባ ምድር መጻተኛው ምን ገጠመው? በሰሜን በኩል ከሴማዊ አገሮችና ከቀይ ባህር ማዶ ከአፍሪካ ቀንድ ባህሎች ጋር ግንኙነት ያላት የመን፣ አሁን በጊዜ ተለዋዋጭነት ተክዳ የመካከለኛውን ዘመን ባህሎች የሙጥኝ ብላለች፡፡
ዓድል በየመን በቆየባቸው ጥቂት ዓመታት መገለልን፣ መድሎንና የእርስ በርስ ጦርነትን ገፈት ቀምሷል፡፡ የሚኮራበት ጠይም የምሥራቅ አፍሪካ የቆዳ ቀለሙ ኋላቀርና ጥንታዊ ከሆነው የየመን ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ እንዳይዋሃድ እንቅፋት ሆኖበት ነበር። ዓድል ይህንን ሁሉ መሰናክል አልፎና የአያት ቅድመ አያቱን ምድር ለቆ፣ ወደ ተሻለ ሀገር መሄድ የቻለው ጠንካራ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ አማራጭ ስለሌለውም ጭምር ነበር።