2 871 419 libros electrónicos en 110 idiomas
¿No le conviene? No hay problema. Puede devolverlo en un plazo de 30 días
No se equivocará con un vale de regalo. El destinatario puede elegir cualquier producto de nuestra oferta.
Política de devolución de 30 días
ወደ እርስዋ ቀርቦ ውኃ አጠጪኝ አላት፤ አባ ጊዮርጊስ "አንተ የሕይወት ውኃ ስትሆን ከሳምራዊትዋ ሴት ውኃን ለመንህ" እንዳለ የሕይወት ውኃ ክርስቶስ ውኃ ለመናት፡፡ እርሱ የተጠማው ውኃ ሳይሆን የእርስዋን ነፍስ ነበረ፡፡ እርስዋም አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሳምራዊት ከምሆን ከእኔ ውኃ ትለምናለህ? አለችው፡፡ እንዲህ ነው ነገሩ፡፡ የቆሰለች ነፍስ ስለ ዘር ታወራለች፡፡ ተስፋ የቆረጠች ነፍስ የዘር ጉዳይ ሲሆን ልሳንዋ ይከፈታል፡፡ ውኃ ለማጠጣት ዘር መጠየቅን ምን አመጣው፡፡ ውኃው አይሁዳዊ ነው? ወይንስ ሳምራዊ? ውኃ ጠማኝ የሚል ሁሉ ውኃ ይገባዋል እንጂ ዘሩ አይጠየቅም፡፡ እርስዋ ግን ጠየቀችው፡፡ በእርግጥ ይህች ሳምራዊት ሴት ይህን ጥያቄ የጠየቀችው ክርስቶስ መሆኑን ከማወቅዋ በፊት ነበር፡፡ክርስቶስ መሆኑን ካወቀች በኋላ ግን ስለ አይሁዳዊነትና ስለ ሳምራዊነት ስትናገር አልተሰማችም፡፡ "አንተ አማራ ስትሆን ጉራጌ ከምሆን ከእኔ ውኃ ለምን ትለምናለህ?" "አንቺ ኦሮሞ ስትሆኚ ትግሬ ከምሆን ከእኔ እንዴት ውኃ ትለምኛለሽ?" በሚል ጥያቄ ሀገሩን ያጨናነቁተ ክርስቶስን ያወቁ ክርስቲያኖች መሆናቸው ግን ልብን የሚሰብር እውነታ ነው፡፡ በዚህ ጠባያችን እንደ ክርስቲያን ሳንኖር እንደ ክርስቲያን ልንሞት መሆኑ ምንኛ ያሳዝናል?
/ከውስጥ ገጽ የተወሰደ/
ይህ መጽሐፍ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ መጣጥፎችን ይዟል፡፡
ክፍል አንድ
ልዩ ልዪ ስብከቶች
የኤፍራጥስ ወንዝ /6/፣ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? /21/፣ የካም ትውልድ /31/፣ ደስ ይበላችሁ /42/፣ ጌታ ሆይ ይህን ውኃ ሥጠኝ /49/፣ በገነት ያሉ ሦስት አስደናቂ ነገሮች /54/፣ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? /55/፣ የትሕትና ትምህርት ቤት /58/፣ እንዴት ወድቀን እንዴት ተነሣን? /66/፣ ሁለቱ መታጠቢያዎች /71/፣ ለማንም እንዳትናገር /74/፣ አባቶቻችን እንዲህ እንዲህ አሉ /79/፣ በሰንበት መፍረስ /91/፣ ዛሬ ነገ ነው? /93/፣ መርጦ መወለድ /96/፣ ኮሜድያኑ ሰማዕት /98/፣ ባለጸጋ ነዳያን /99/፣ ስሞት ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን? /105/፣ የግርፊያ ሰልፍ /110/፣ ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብታቸው /117/፣ ቤተ ክርስቲያንና ሚሽነሪዎች /121/
ክፍል ሁለት
የበዓላት ስብከቶች
ዘልደት
የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? /126/
ዘጥምቀት
መጥምቁ ዮሐንስን ማን አጠመቀው?/131/
ታኅሣሥ ገብርኤል
ከክርስቶስ በፊት የነበሩ ክርስቲያኖች /140/
ጾመ ነነዌ
ጣዕም የሌለው ስብከት /151/
ዘኒቆዲሞስ
በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጣ /158/
ዘሆሳዕና
ንጉሥ በአህያ ላይ /161/፣
የትንሣኤ ስብከቶች፣
፩ አትክልተኛ መስሏት ነበር /164/፣ ፪ ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ /171/፣ ፫ ፍቅር ቁስል ነው /178/
ዘጰራቅሊጦስ
የግንቦት ልደታ
የደብረ ታቦር ስብከቶች
¡Hola! Soy Libroamiko, tu asesor de libros.
¿Cómo puedo ayudarte?